ወያኔ በሻለቃ አድማሱ መላኩ የፈጸማቸው ዘጠኙ ድብቅ ደባዎች

Written on Sunday, August 3rd, 2008 at 2:50 pm by ethioforum

(እውነቱ ተሠማ ከአዲስ አበባ) [PDF]  - ማሳሰብያ ይህ ጽሁፍ ለ EMF የተላከው ከአንድ የ KIC ከፍተኛ አመራር ነው :: - በውል እንደሚታወቀው የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) ተልዕኮውን ፈጽሞ ታሪካዊ ኃላፊነቱን ለመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አስረክቧል፡፡ በመቀጠል ደግሞ በዋናነት በመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅትና በሌሎች ሦሥት ፓርቲዎች የተገነባው ቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ መስከረም 14 ቀን 1998 ዓ.ም በውህደት ተመሥርቷል፡፡

በዚህ ታሪካዊ ሂደት ከመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት ምሥረታ ወቅት አንስቶ እውነተኛ የኢትዮጵያ ልጆች ይዘው የተነሱትን ሕዝባዊ ዓላማ ለማክሸፍ በቀበሮ ባህታዊነት ያደፈጡ ቦርቧሪዎች እንደነበሩ ይታወቃል፤ ከመካከላቸው አንዳንዶቹ ሥራቸው አጋልጧቸው በመንገድ ላይ ተተፍተዋል፡፡ የሠሩት ወንጀል አስበርግጓቸው ማንም ሳያባርራቸው የፈረጠጡም ነበሩ፡፡ የተቀሩት ግን ድብቅ አጀንዳቸውን እንደ ያዙ በእውነተኛ የኢትዮጵያ ልጆች መካከል አድፍጠው እስከ ቅርብ ጊዜ ሊኖሩ ችለዋል፡፡ ከእነዚህ ድብቅ አጀንዳ አራማጆች አንዱ ሻለቃ አድማሱ መላኩ ናቸው፡፡

ዛሬ ስለ እኚህ ሰው ማንነት አንዳንድ ነጥቦችን ለማንሳት የፈለኩት ለረጅም ጊዜ በቅርበት ስለማውቃቸውና በህዝብ ላይ እየፈፀሙ ያሉትን በደልም አላቆም ስላሉ ሰዎች ማንነታቸውን ተገንዝበው እንዲጠነቀቁአቸው ለማሳሳብ ነው፡፡ በአሁኑ ወቅትበውጭ አገር ተቀምጠው መልካም ምግባር ያላቸው አስመስለው የሚያነበንቡትን የእኚህን ሰውዬ ማንነት ሁሉም እንዲያውቀው ማድረጉ ተገቢም አስፈላጊም ሆኗል፡፡

ድርጅቱ ቦርቧሪነታቸውን ተገንዝቦ እርምጃ ይወስዳል ብዬ ለረጅም ጊዜ ስጠብቅ ከነአካቴው ወደ ውጭ አገር ላካቸው፡፡ ሻለቃ አድማሱ መላኩ በግንቦት 8 ቀን 1981 ዓ.ም በተሞከረው መፈንቅለ መንግሥት ተሳትፈዋል፡፡ በሕይወት መናቸው ሁሉ እንደ ምሥጥ ውስጥ ለውስጥ ከመሄድ በስተቀር አንድም ጊዜ በልበ ሙሉነት አንድን ነገር የመጋፈጥ ወኔ ኖሯቸው አያውቅም፡፡ በመሆኑም እኚህ ሰው መፈንቅለ መንግሥቱ እንደ ከሸፈ ይርበተበቱ ገቡ፡፡ በወቅቱ የነበረው መንግሥት ደግሞ የእኚህን ሰው ደካማ ጎን ልብ ብሎ አስተዋለ፡፡ ከዚህ በመነሳት እሳቸውን ከመግደል ወይም ከማሰር ይልቅ በመረጃ ምንጭነት መጠቀምን መረጠ፡፡ እሳቸውም የተጠየቁትን ሁሉ ዘከዘኩ፡፡ በእሳቸው መረጃ ሰጭነት ከበታች ሹማምንት እስከ ጄኔራል መኰንኖች እየተያዙ ታሠሩ፡፡ብዙዎቹም ተረሸኑ፡፡ አንዳንዶች አገር ጥለው ተሰደዱ፡፡ ሻለቃ አድማሱ መላኩ ግን ይህ የክህደት ተግባራቸው እንደ ውለታ ተቆጥሮላቸው ወዲያው ተለቀቁ፡፡ ከእስር ቤት ጥለውን ወጡ፡፡ በእሳቸው መረጃ ሰጭነት ከተያዙት ብዙዎች ለዓመታት ታሰሩ፡፡ ጓደኛቸው በመሆኔ ይህን በቅርብ በሚገባ አውቃለሁ፡፡ በክሕደት ተግባራቸው ጓደኞቻቸውን አስቀብረው በሕይወት ቀርተው ሕይወትን አጣጣሙ፡፡ አንድ በሉ!

ስለ እውነት በእውነት እንነጋገር፡፡ ሻለቃ አድማሱ ጥቅም እስካገኙበት ድረስ ለሰው ልጅ ጤነኛ ኅሊና ተቃራኒ የሆኑ ማንኛውንም ዓይነት እኩይ ድርጊቶች ይፈፅማሉ፡፡ ፈጽመዋልም፡፡ ለዚህም ማስረጃዎች አሉኝ፡፡ እስቲ እንመልከት፡፡ ወዳጅም ሆነ ጠላት በውል እንደሚያስታውሰው በዚህች ለዘመናት ታፍራና ተከብራ በኖረች ጥንታዊት አገር ላይ ዘረኞች የጎሣ መርህ ሥርዓተ - አገዛዝ እንደ ዘረጉ ለሺህዎች ዓመታት ተከባብረው የኖሩት የኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ብሔረሰቦች በአማራ ሕዝብ ላይ ክንዳቸውን እንዲያነሱ ከፍተኛ ቅስቀሳ ተደርጓል፡፡

በዚህ ምክንያት አንዳንድ የጠላት መሣሪያ የሆኑ ቡድኖችና ግለሰቦች በንፁሐን የአማራ ልጆች ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ችለዋል፡፡ በተጓዳኝም የኢትዮጵያ ሕልውና መቀጠሉ አጠራጣሪ ሆነ፡፡ እንግዲህ በእነኚህ ተጨባጭ ምክንያቶች በክቡር ፕሮፌሰር ዓሥራት ወልደየስና በሌሎች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ተነሳሽነት የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) ሊመሠረት በቃ፡፡ መዐሕድ እንደተመሠረተ ሻለቃ አድማሱ መላኩ በድርጅቱ ውስጥ በተላላኪነት ተቀጠሩ፡፡ አንድ ከፍተኛ ኰንን ድብቅ አጀንዳ ከሌለው በስተቀር እንዴት በተላላኪነት ሊቀጠር ይችላል? ተላላኪ የመሆናቸው ነገር በወቅቱ ብዙዎቹን አነጋግሯል፡፡ ዓላማቸውን በኋላ ደግሞ በተግባር አሳይተዋል፡፡

የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መአሕድ) እንደተመሠረተ የኢትዮጵያ አንድነትና የዴሞክራሲ ጠላቶች የድርጅቱን ሕልውና ለማጥፋት ከፍተኛ ክትትል ማድረግ ጀመሩ፡፡ መሪውን ክቡር ፕሮፌሰር ዓሥራት ወልደየስንም ይዘው አሠሩ፡፡ አንገላቷቸው፡፡ በቂ ሕክምናም እንዳያገኙ አደረጓቸው፡፡ የሕግ ልዕልና በጠብመንጃ ኃይል በተደፈጠጠበት አገር ፍትሕ ያለ ለማስመሰል ነጋ ጠባ ወደ ፖለቲካ ፍርድ ቤት አመላለሷቸው፡፡ በደረቅ ወንጀል ከታሠሩና በማኅበራዊ ሕይወታቸው ለመልካም ሥነ-ምግባር ተቃራኒ የሆኑ ድርጊቶችን ከፈፀሙ እስረኞች ጋር ባንድ ቤት ውስጥ በማሠር ሞራላቸውን ጭምር ተፈታተኗቸው፡፡ ጠላት በክቡር ፕሮፌሰር ዓሥራትና በትግል አጋሮቻቸው ላይ ይህን ሁሉ ግፍ መፈፀሙ ላያስደንቀን ይችላል፡፡ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና የአንድነት ኃይሎች ሁሉ ያፈሩበት ግን በሻለቃ አድማሱ መላኩ ድርጊት ነው፡፡

ሻለቃ አድማሱ መላኩ በሥራ አጋጣሚ በእጃቸው የገቡትን ለጠላት ጠንካራ መረጃ የሚሆኑትን በርካታ የፓርቲውን ሰነዶች ወስደው ለአቃቤ ሕግ ዘረገፉ፡፡ የአማራ ሕዝብ ልጆች በአደባባይ በግፍ በሚገደሉበት በዚያ በጨለማ ወቅት እንደዚህ ዓይነት ከፍተኛ ክሕደት ፈጸሙ፡፡ በጊዜው የፓርቲው አባል ብቻ ሳይሆኑ ለእሳቸውና ለቤተሰባቸው መተዳደሪያ ደመወዝ ጭምር ይከፈላቸው እንደነበር ሳስታውስ ደግሞ ግለሰቡ የእናት ጡት ነካሽ መሆናቸውም ጎልቶ ይታየኛል፡፡ እንግዲህ ልብ በሉ! ሻለቃ አድማሱ መላኩ ክቡር ፕሮፌሰር ዓሥራትንና የትግል አጋሮቻቸውን ለማሰቀል የሰነድ ማስረጃዎችን ለጠላት ያቀበሉ ግለሰብ ናቸው፡፡ ሁለት በሉ!

የኢትዮጵያ ሕዝብ በውል እንደሚያስታውሰው የዛሬዎቹ ገዥዎች ሥልጣን ላይ ከወጡ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው ምርጫ ኢ ዴሞክራሲያዊ ነበር፡፡ በሁሉም መልኩ የምርጫን ሕግ የሚቃረን እንደ ነበር አይረሣም፡፡ በዚህ ምክንያት የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) ምርጫውን አቋርጦ መውጣት ግድ ሆነበት፡፡ በሁለተኛው ምርጫ ወቅት ግን የመላው አማራ ሕዘብ ድርጅት (መዐሕድ) ራሱን ከምርጫ ለማግለል አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ድርጅቱ በምርጫው ሳይሳተፍ ቢቀር ገዥው ፓርቲ ሰበብ ፈልጎ የድርጅቱን የሕጋዊነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት ይሠርዝ ነበርና ነው፡፡ ስለዚህ ድርጅቱ ሕጋዊነቱ እንደተጠበቀ እንዲቆይለት ብቻ ጥቂት አባላትን ከጽሕፈት ቤቱ በእጩነት አቅርቦ አስመርጧል፡፡ ሻለቃ አድማሱ መላኩ ከተመረጡት አንዱ ናቸው፡፡ እሳቸው ግን ያጋጠማቸውን የመመረጥ ዕድል በመጠቀም ለፓርቲው ከመሥራት ይልቅ ለገዥዎች ጉዳይ አስፈጻሚ ሆነው ሲያገለግሉ ተስተውለዋል፡፡ በመዐሕድ ውስጥ ሠርገው የገቡ የገዥው ፓርቲ ቅጥረኞችን በማስተባበር መዐሕድን ለማነቅ ከፍተኛ ሚና መጫወታቸውንም ወዳጅም ሆነ ጠላት በውል የሚያውቀው ጉዳይ ነው፡፡ ሦስት በሉ!

ግለሰቡ የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መዐሕድ) ተልዕኮውን በሚገባ ፈጽሞ ወደ መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ሲቀየር በከፍተኛ ደረጃ ተቃውመዋል፡፡ የፓርቲው ስም ተቀይሮ በዜጎች መካከል በዘር፤ በቋንቋና በሃይማኖት ልዩነት ሳይደረግ ሁሉም ለአገሩ አቅም በፈቀደ ሁለንተናዊ አስተዋጽኦ የሚያበረክትበት ሁኔታ መፈጠሩ ለያዙት ድብቅ አጀንዳ መንገዱን እንደሚዘጋባቸው አውቀዋልና፡፡ ሆኖም በግልፅ ወጥተው በአፍራሽ አቋማቸው ለመግፋት ወኔ አልነበራቸውም፡፡ ስለሆነም አድፍጠው ፓርቲውን እየቦረቦሩ ጊዜ ለመግፋት ወሰኑ፡፡ አራት በሉ!

ሰውዬው በፓርቲው ውስጥ ባለማቋረጥ ደባ እየፈጸሙ መሆናቸው ቢታወቅም አውቀው እንደሚመከሩ በመገመት ለብዙ ዓመታት በትዕግስት ሲታለፉ ኖረዋል፡፡ ሆኖም አንዴም የታረሙበት ወቅት አልነበረም፡፡ እኚህ ሰው መኢአድ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጥምረት በቅንጅት ስም በተንቀሳቀሰበት ወቅትም አፍራሽ አቋም ከማንፀባረቅ ወደ ኋላ አላሉም፡፡ የፓርቲው የሰሜን ቀጣና ኃላፊ ሆነው እንዲሰሩ በተመደቡበት ወቅትም በርካታ ጠንካራ አባላትን አሳስረዋል፡፡ አስገድለዋልም፡፡ እጅ ከፍንጅ ግን አልተያዙም፡፡ የሆነውን ሁሉ ግን ሕዝቡ በሚገባ ያውቀዋል፡፡ ህዝቡ በጊዜው ለማዕከል ሪፖርትም አድርጓል፡፡ ይህ እንግዲህ የሻለቃው አምስተኛው   እኩይ ድርጊት ነው፡፡

ሻለቃ አድማሱ መላኩ በ1997 ዓ.ም በቅንጅት ስም ለተወካዮች ምክር ቤት ከተመረጡት ሰዎች አንዱ እንደነበሩ ይታወቃል፡፡ በወቅቱ የፓርቲው ላዕላይ ምክር ቤት ለደሞክራሲ መስፈን አስፈላጊ የሆኑ ስምንት ነጥቦች ካልተሟሉ ፓርላማ ላለመግባት ባንድ ድምፅ ወሰነ:: የገዢው ፓርቲም የቅንጅት አመራሮችን ሲያስር ሻለቃ አድማሱን ግን ሳያስር ተዋቸው፡፡ ነገር ግን እኚህ ግለሰብ ስልክ እየደወሉ ተመራጮች ሁሉ ፓርላማ እንዲገቡ ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል፡፡ ለፓርቲው ውሳኔ የማይገዙ ከሃዲ መሆናቸውን በዚህ ድርጊታቸው ራሳቸው በራሳቸው ላይ መስክረዋል፡፡ ስድስት በሉ!

ከሁሉም በላይ የአመራር አባላት አብዛኞቹ ሲታሠሩ ሻለቃ አድማሱ ሳይታሠሩ የቀሩበት ምክንያት ብዙዎችን አነጋግሯል፡፡ ብዙ ታዛቢዎች የገዥው ፓርቲ የውስጥ አርበኛ በመሆናቸው ሳይታሠሩ መቅረታቸውንም ይናገራሉ፡፡ በተለይም ከምርጫው በኋላ ጭልጥ ብለው ለሥርዓተ-አገዛዙ አገልጋይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሰባት በሉ!

ሰውዬው ውጭ ሀገር የሄዱት በፓርቲው ገንዘብ እንደነበር ይታወቃል፡፡ እዚያም የሚኖሩት በፓርቲው ገንዘብ ነው፡፡ ታዲያ እንዴት የፖለቲካ ጥገኝነት በቀላሉ ሊያገኙ ቻሉ? ለገዥው ፓርቲ በምሥጢር በሠሩት ውለታ መሆኑን መጠራጠር የለብንም፡፡ እንዴ? ስምንት እንበል፡፡ ሻለቃ አድማሱ መላኩ የፈጸሟቸው እኩይ ድርጊቶች ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም፡፡ በጣም በዝርዝር ሳንገባ በእምቁ ለማስቀመጥ መርጬአለሁ፡፡ ለማነሳቸው ጭብጦች ሁሉ በቂ መረጃ አለኝ! ጥያቄ እስቲ ላንሳ፡፡ ከአመራር አባላት አንዳንዶቹን እየጠቆሙ ያስያዟቸው እኚህ መኰንን መሆናቸውን ስንቶቻችን እናውቃለን? ዶክተር ታዴዎስ ቦጋለን፤ አቶ አሰፋ ሀብተወልድንና ሻለቃ አርጋው ካብታሙን አስይዘዋል፡፡ እነዚህ ለምሳሌ ተጠቀሱ እንጅ ሌሎች በርካቶችንም አስይዘው ማሳሰራቸውን ይታወቃል፡፡ ብዙ ሰው ይህን እውነታ ላያውቅ ይችላል፡፡ ግን እውነት ነው፡፡ ተጨባጭ ማስረጃ አለኝ፡፡ አንዲህ ዓይነት ከሃዲ ግለሰብ ናቸው ሻለቃው፡፡ ዘጠኝ በሉ!

ሻለቃ አድማሱ የቅንጅት አመራር አባላት ከታሠሩ በኋላ ድብቅ አጀንዳቸውን ተፈጻሚ ለማድረግ በስፋት ተንቀሳቅሰዋል፡፡ የአዲስ አበባ ተመራጮችን ለገዥው በሚመች መልኩ አስተዳደሩን እንዲረከቡ ከፍተኛ ቅስቀሳ አድርገዋል፡፡ ዛሬ ‹‹የቅንጅት ስምና አርማ ባለቤት እኛ ነን፡፡›› የሚሉት እነ አየለ ጫሚሶ እንዲፈጠሩ ከገዥው ፓርቲ ጋር እጅና ጓንት ሆነው ሠርተዋል፡፡ሻለቃ አድማሱ የቅንጅት አመራር አባላት በእስር ቤት በነበሩበት ወቅትወይዘሮ ሳባ መኰንን የተባሉትን ጠንካራ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ አባል ‹‹ኢንጅነር ኃይሉ መኢአድን በአዲስ መልክ አደራጁ! ብለዋል›› በማለት ለማሳሳት ሞክረዋል፡፡ ወይዘሮ ሳባ ግን ይህን አሳሳች መልዕክታቸውን ስላልተቀበሏቸው ለአገዛዙ የፀጥታ አባላት ጠቁመው ለሦስት ወር በሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ አሳስረዋቸዋል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ ከጎጃምና ጎንደር አዲስ አበባ የመጡ የፓርቲ ተጠሪዎችን በምሥጢር ጠቁመው አስይዘው አስደብድበዋል፡፡

የአመራር አባላቱ እንደታሰሩ እውነተኛ ኢትዮጵያውያንን እየጠቆሙ ለማስያዝ እንዲመቻቸው ወዲያው ጸጉራቸውን አጎፍረው፣ጺማቸውን አሳድገውና ጥቁር መነጽር አድርገው የቀበሮ ባህታዊ ሥራቸውን ፈጽመዋል፡፡ ከውጭ አገር ከፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች ለእስረኞች ቤተሰብ የተላከውን ገንዘብ ከመሰሎቻቸው ጋር ተቀራምተዋል፡፡ ሻለቃው እንዲህ ዓይነት ሰው ናቸው፡፡ ጥቅማቸውን ብቻ ማዕከል አድርገው ይንቀሳቀሳሉ፡፡ ብዙ ጊዜ የአማራ ሕዝብ ልጅ መሆናቸውን ይናገራሉ፤ ለዚህ ሕዝብ ግን ክብርና ፍቅር አሳይተው አያውቁም፡፡ ይልቁንም የባለቤታቸው ወገን ለሆኑት ለኤርትራ ተወላጆች ትልቅ ከበሬታ ይሰጣሉ፡፡ ለትግራይ ተወላጆች ደግሞ ባሁኑ ወቅት የኪስ መሐረብ ሆነዋል፡፡ ወሎዬ መሆናቸውን ማንም ያውቃል፡፡ እሳቸው ግን በደረሱበት ሁሉ ጎንደሬነታቸውን ያውጃሉ፡፡ እሳቸው ብቻ በሚያውቁት ምክንያት ወሎዬ መሆናቸው ያሳፍራቸዋል፡፡

አሁን ደግሞ በውጭ አገር ይገኛሉ፡፡ ምናልባት በኢትዮጵያዊነታቸው ሳያፍሩ ይቀራሉ? የሻለቃ አድማሱ መላኩ የግል ኑሮ በግልፅ ከሚታወቀው ገቢአቸው በላይ ነው፡፡ ብራዚሊያ ቮልስዋገን ታርጋው 30667 የሆነ መኪና አላቸው፡፡ እንዲሁም የኤርትራ ተወላጅ የሆኑት ባለቤታቸው ፊያት ሌተስት መኪና ያላቸው ሲሆን ባሁኑ ወቅት በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጣቢያ በኃላፊነት እርከን ላይ ይሠራሉ፡፡ ልጃቸው ዳዊት አድማሱ በቅርቡ ባልታወቀ ሁኔታ በአዲስ አበባ ንግድ ባንክ የኃላፊነት ቦታ ሊይዝ ችሏል፡፡ ንፁሕ ኢትዮጵያውያን ዛሬ ከሥራ ያለ ምክንያት ሲባረሩ የእኚህ ሰውዬ ልጅ ግን ያለ ደረጃው የኃላፊነት ቦታ አግኝቷል፡፡ ቀደም ሲል የፓርላማ አባል በነበሩበት ወቅት የተሰጣቸውን ቤት እስከ አሁን እንዲመልሱ አልተደረጉም፤ ቤተሰቦቻቸው ይኖሩበታል፡፡ ይህ ሁሉ የተደረገላቸው ንፁሃንን እያሳሰሩ ለእንግልት ስለዳረጉ የደም ዋጋ ክፍያ ይሆን? በአስኮ አካባቢ ግራውንድ ፕላስ ዋን ሕንፃ እየሠሩ መሆናቸውም ታውቋል፡፡ ገንዘቡን ከየት አመጡት? ለእስረኞች ቤተሰብ በተላከው ገንዘብ መሆኑን ብዙዎች ይናገራሉ፡፡ ሆነም ቀረ በሥርዓተ አገዛዙ በምሥጢር እስከሰሩ ገንዘብ እንደማይቸግራቸው ግልፅ ነው፡፡

እኚህ አይረቤ ሰው ባሁኑ ወቅት በውጭ አገር እውነተኛ ኢትዮጵያውያንን አሳስተው የአገዛዙ ሹማምንት የሰጧቸውን የአሽከርነት ሥራ ከግብ ለማድረስ እንደሚንቀሳቀሱ ታውቋል፡፡ በተለይም ሰኔ 14 እና 15 ቀን 2000 ዓ.ም የተካሄደው የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ 1ኛ መደበኛ ጉባዔ በስኬት መጠናቀቁ አንገብግቧቸዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ፓርቲውን ለማፍረስ የአቅማቸውን ያህል እንደሚፍጨረጨሩ ደርሰንበታል፡፡ እርግጥ ነው የአእምሮ ችግር ያለበት ሰው ካልሆነ በስተቀር እኚህን ከሀዲ ግለሰብ የሚከተላቸው የሚኖር አይመስለኝም፡፡ ሆኖም ጥቂት የዋሆችን ‹‹የቅንጅት ላዕላይ ምክር ቤት አባል ነኝ›› በማለት ለማሳሳት አቅም እንደማያጡ አውቄአለሁ፡፡ ስለዚህ ከበቂ በላይ ስለእኚህ ሰውዬ መረጃ አቅርቤአለሁ፡፡ ማንነታቸውን በውጭ አገር የሚገኙ ወገኖቻችን ሁሉ በሚገባ ማወቅ ይኖርባቸዋል፡፡ ሻለቃ አድማሱ መላኩ ለራሳቸው ብቻ የሚኖሩ ሰው ናቸው፡፡

ዛሬ ከአገር ቤት ርቀው የሚገኙ ወገኖቻችንን ለማሳሳት የሚሞክሩት ማንነታቸውን እንደማያውቁ በመገመት ነው፡፡ ‹‹ጅብ በማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል›› ይባል የለ? ያም ሆነ ይህ እውነተኛ የኢትዮጵያ ልጆች ሁሉ እኚህ የቀበሮ ባህታዊ ራሳቸውን እንዲጠብቁ አበክሬ እመክራለሁ፡፡

Related post:

  • No related posts
  • 58 Responses to “ወያኔ በሻለቃ አድማሱ መላኩ የፈጸማቸው ዘጠኙ ድብቅ ደባዎች”

    1. zulu Says:

      Well said:

      I think the writer has exposed some of the old thugs who lived up on the people of Ethiopia through timeout like bugs. We have to clean up the opposition party with clear mandate based on principles and the rule of law.

      I am very glad that the writer brought up few among the many, and I think that is the tip of the iceberg. Let us see things wisely and clean our dirt off our thoughts and move forward with rule of law and principle as our base.

    2. maru Says:

      እግዚኦ ነው ማለት:: ለመሆኑ አቶ ሃይሉ ሻወል ይህንን እያወቁ ነው ይህንን ክፉ ሰው “ለማስታረቅ” ብለው የላኩት::

      አሁን እውነት እየወጣ ነው::

    3. dawitsj Says:

      እሳችው ያው አይደሉ

    4. Anonymous Says:

      ወይ ጣጣ !!! ማንን ልምን ?

    5. Gen shoaregede gedele Says:

      The whole history is based on facts. Hodam admasse is responsible for prof Asrat and so many Amhara’s innocent children who are being killed by TPLF.HODAM admasse will pay the highest price at the end of his bosses. What is very intersting is another hodam hailu shawul has the same history with hodam admasse. Hailu shawul has been working with weyane still now. Hodam admasse was behind abayineh birhanu’s captured and arrested by weyane. Any ways all hodam dogs who are under the leadership of hodam and conscienceless hailu will expose one by one.

    6. Fekadu Says:

      where is the evidence?also where were you ?why you preafer this day to expose him? to be honest,i couldn’t find one evidence clearly.all points are based on TIRITARE.I’m sorry to say this,the article is full of ALUBALTA.unless the writer is also accountable.because,we didn’t hear nothing before about Shaleka Admasu before.
      you said:-and belu,….hulet belu……sebat belu…but you don’t have one tangeble point.you gave us dozen of garbage in the name of information.
      this is anti democratic and evil.
      please keep quit!!!

    7. Dilassema Says:

      በኢትዮጵያ ታሪክ የገደላት እንጅ የሞተላት ተጠቅሞም አያዉቅ ስለዚህ ሻለቃ ከገዳዮች አንዱ ስለሆኑ ታሪክ ይፋረዳቸዉ :: ይህም አልበቃ ብሎአቸዉ በቅንጅት ላይም የፈጸሙትም ካለፈው የከፋ እንጅ ያነሰ አይደለም:: ከአሁን በሆአላ ህዝባችሂን እኒህን ክሃዲ ሞላጫ ሌባ ተጠንቅቆ መጠበቅ አለበት

    8. megen Says:

      Isn’t this too late ????

    9. almaze Says:

      ሃይሉ ሻውል ይሕንን እያወቁ አይደል ሻለቃው ብርሃኑ ነጋን ስለሚጠላ በቻ እሱን ልከው ቅንጅትን ያስፈረሱት:: እግዚአብሔር ለሁሉም ብድራቸውን ይስጣቸው::

    10. Surafel Says:

      Dear EMF,

      I have met ShaleQa Admasu once or twice and it is obvious the guy is very slippery. I also suspect that he has some sort of arrangement with the TPLF. The fact that even though he didn’t join parliament but still enjoys a free government house is extremely suspicious. There were also rumors regarding his handling of documents.

      Getting back to this article though, I am amazed that you guys are printing innuendos and conjunctures as facts. The writer continuously assures as that he has solid evidence and facts about this or that and plays fast and loose with sweeping assumptions with a countdown. The writer and EMF need to understand that stating he did this or that remains a rumor unless backed by a fact. I don’t see any fact or evidence aside from the litany of accusations. If the writer has any evidence, why doesn’t he forward them to EMF so that we could all read it? I hate the KIC and extremely suspicious of ShaleQa Admasu, but this article does not prove or disprove anything. This is just rumor and hearsay, plain and simple.

    11. shewangezaw Says:

      ሻለቃ ጌታቸው መንግስቴም ሌላው ህዝብ ያላወቀው ድርጅት አፍራሽና ሴረኛ ሰው ነው

    12. Anonymous Says:

      እኔ ሰውየውውን ድሮውንም አላምናቸውም ነበር:: የወያኔ ሚስጥርኛ ናቸው ሻለቃ አድማሱ መላኩ::

    13. shewangizaw Says:

      ሻለቃ ጌታቸው መንግስቴም ከዚሀ ያልተናነሰ ተሊኮ ያለው ሀዝብ ያልደረሰበት አንድ ቀን ይፋ የሚወጣ ችግር ያለበት ግለሰበ ነወ ለሁላቸሁም የሰራችሁን ይስታቹ

    14. WOY GUD Says:

      What kind of evidence is this? I have read this writing with interest. As I was reading it I could not help question the motive of the writer. It is clear there is no convincing evidence supported with iron clad facts. It is clear to an objective reader that it is all innuendos and very loose argument. I really thought someone is out to tag him as an agent. In today’s Ethiopian politics of “atfito metifat” I am not surprised.

    15. snshaw Says:

      ስለሽለቃ አድማሴ የተጻፈውን ስመለከት ያው የተለመደ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንጂ የተለየ ነገር አላየሁበትም::እንደዚህ የመሳሰለውን ዘመቻ ባለፉት 2 አመታት በተለይ በሰፊው ሲሰራበት አይተናል ማን ምንነቱን ግልጽ ሳያደርግ በመሰለው አካሄድ የግለሰቦችን ስም ሲያጎድፍ መመልከት መለመዱ ብቻ ሳይሆን ይህንን የመሰለ አጸያፊ አካሄድን በመረጃ ላይ ያልተመሰረተ ነው ብለን ለመጠየቅ ያለመሞከራችን ምን ያህል በብዥታ ውስጥ መዘፈቃችንን የሚያሳይ ነው:: ችግሩ ያለንበት ወቅት ያመጣብን ጣጣ በመሆኑ ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል እንደሚባለው እነዚህን የመሳሰሉ ውርደት ሸመቻን ሆኖ እንድንገፋ የሚማስኑልን ስም አጥፊዎች ሀይ የሚላቸው እስኪመጣ መግፋት የግድ ነው::
      አምላክ አገራችንን ኢትዮጲያን ይጠብቅ!!
      ስንሻው

    16. Mamo Dimocratu Says:

      where were the writer for the last years?why he stay a long time in silent? not only this,but also i can’t see one information based on evidence among the nine points listed above.
      -Shaleqa is living in government house ,he was not in prison with cud leaders despite he didn’t attend the parlama…his son is working in comercial bank on the good position…bla bla..bla…are not an evidence for his conspirecy or BORBUARINET.the all points mentioned above are TERA ALUBALTA.everybody!please evaluate the mentioned points again and again carefully.i hope,no body can find one factual point rather than BADO ALUBALTA.

    17. Mamo Dimocratu Says:

      Dear Editor,
      why not allowed your site{forum]for free opnion &comment? i send my coment now,but it is not posted there? why?

      Mamo Dimocratu

    18. Kibret Says:

      It appears that the tantrum was sent to EMF for publication by Dr Taye Woldesemayat. Dr Taye has been doing himself a great disservice to himself and others by stooping too low. Sad!!!!!!!!

    19. wow Says:

      hi guys Shalka Admasu, Eng Hailu, Dr Taye…all are the same…in any way we know them very well so dont worry…….we will continue forword…this guys did a lot of things for the past 30 years now we need new face,…young leaders…like W/t Brtukan…so they are like EPRP….
      God Bless Ethiopia!!!!!
      Death for Weyane+Melese…and other bandas

    20. Fikre Hizb Says:

      I can only second Surafel in that though I do not like KIC and extremely suspicious of ShaleQa Admasu, “but this article does not prove or disprove anything. This is just rumor and hearsay, plain and simple.”

      I want to have facts even for accusations of people, whom I do not like. We have to learn to be fair and very objective based on facts to every person and every organization. Confirmation of our suspicion could not and should not replace facts and objectivity.

      Thanks.

    21. Mike Says:

      It is distructive to publish such articles that is not supported by hard facts. Shaleqa Admasu might or might not be as the writter said. People have different undertanding. Some take the article seriesly where as others rubish it. As a fair and reasonable person i am not happy to consume such an substantiated rumors.
      EMF please step up and be true media people

    22. bancharaow Says:

      I thold for many people just logic and comman saynce Now I am the winer my logic works He is an evel

    23. abeba Says:

      this is too late writer; where have you been?
      this is hailu sahwel & his gang’s headache. we can’t come back to this matter now.

      people, it might be an excuse for KIC for the destruction they made.

      me, i don’t believe any thing that comes from KIC & co.

    24. The Insidere from Dispora Says:

      First I would like to start from the above two persons comment “woy Gud and Snshaw those two individuals are the woyanne tags. We have known them playing the woyane agents roll in different comment secition of Ethiopians web sites. Also they have known making a pro woyane comments throught Paltalk like ECADF and etc..
      Going back to the orginal letter came through EMP, there are disturbing facts such as why the writer waited this long to share the story about this kehadi or traitors. I mean when we are exposing about Saleqa. Admasse and Dr. bezabeh better known Dr. Bezebez delegation to come to America with the approval of Woyane, Yamamoto (us ambssador in Addis Abeba) and Eng. Hailu Shawel? We new since January 2006 Saleqa. Yosef Yazew, Eng. Moges Brook and So called Dr. Seyume Solomon, Solomon Bekele (another fake millioner woyane agent) has been working through State Department while Yamamoto was still in State Department. The main reason why woyane kept the kinijit leaders such a long time till he bought and convence Eng. Hailu Shawel himself and family members through Yamamoto at Kalite prison cell. Once Hailu Shawell is conviced to sell out the People trust, Yamamoto and Melese suggested to Hailu Shawel to recomand Saleqa. Admasse and Dr. Bezabeh to come to America and help resolve Kinijit issue. Of course, Hailu when he was in the hospital he got informed by woyane to he could get a visa through Yamamot for those two individuals. Shaleqa. Yosef yazew’s wife went to Ethiopia with a lot of gift first to discuss the plan with hailu shawel wife, and his wife sister and shaleqa Admasse how to arrange a visa and left a lot of dollor to bribe as much as AEUP associate including Saleqa. Getachew Mengeste wife and kids. Right after that, Shaleqa Yosep Yazew traveled quicklly to Kenya with the organization money worth close to $50,000 us dollors to pay for shaleqa Getachew Mengeste wife and 5 kidds to stay at nice hotel and food for two three month worth of stay while they are provided a document by woyane that they had a dengeres situation for their life staying in Ethiopia through Shaleqa Admasse. Shaleqa Admasse took the documents to shaleqa Yosef hotel with shaleqa Getachew Mengeste’s familly to kenya. They imedetlly regester through UN to get refeuge status. Once they got aproved the refuge status, they left Kenya. I beleived at this moment they came to Cananada or US cities. So the bottom line is all Eng. Hailu group was working from US cities to Ethiopia to kill the strugle through Yamamot and woyanne. Everything we see now around Eng. Hailu groups are not a considence. It is a sold out of kinijit in general. Right after they got relesed from kalite prison, two hours later the woyane’s security agent said “you will see now Eng. Hailu will be the first one will be expeled from kinijit to woaynes supporter in public. Sure enough, Eng. Hailu was busy holding a meeting at his house to dismantle kinijit for two months. He just came to USA to protect and secured his tags from getting expose to public. If it is needed, we will provide more information. Eprp and Dr. Taye was assigned to do the rest of dismantiling kinijit at Diaspora!!!!!
      The rest is HISTORY!!!!!!!!

    25. tesf Says:

      The Insidere from Dispora:
      Those who sided with Shaleqa are nonsense woyane thugs. The truth is in their face. No lies can hold TPLF any more. Poor Yamamot is exhausted trying to establish fake party!!!!!I see him running for his life to where he came from in 1 year, maximum. Go G7
      Cheers,
      ( Yemainega meselote kekotu arach)

    26. tesf Says:

      The Insidere from Dispora:
      Those who sided with Shaleqa are nonsense woyane thugs. The truth is in their face. No lies can hold TPLF any more. Poor Yamamot is exhausted trying to establish fake party!!!!!Go G7
      Cheers,

    27. Anonymous Says:

      ስለስዉየው (ሻለቃው) የማዉቀው ነገር የለም::
      ጸሀፊው ግን ደጋግሞ “ጠንካራ ማስረጃ” አለኝ ከማለት ያለፈ ሲለጽሁፉ ክስ በቂ ማስረጃ አላቀረቡም::
      ማስረጃ የለለው ክስ ክስም ማጥፋት የዘለለ እርባና የሚኖረው አይመስለኝም:: ፀሓፊው ሻለቃውን “አቋሙን በግልጽ የማይገፋ….” ፈሪ አድርገው ሲያቀርቡ እርሳቸው ስማቸውን ለመግለጽ አለመድፈራቸው ያስደንቃል::
      ግልጽነትና ተጠያቂነት እንዲጎለብት ከሆነ ሌላውን ከመክሰሳችን በፊት መጀመሪያ ስለእራሳችን ግልፅ መሆን ያለብን ይመስለኛል::

    28. hodyebasew Says:

      አንድ እግር በርበሬ መንቀል አቅታአቹ እንዲህ አቃጥሎ አንገብግቦ ይፍጃችሁ:: ህዝብ ከጎናችሁ ነዉ እናንተ ገን ተባብራችሁ ወያነን ማስወገድ አቃታችሁ:: እርስበርስ መነካከስ ጀመራችሁ::

    29. Hanni Says:

      I often saw Mr. Admasu having a drink with some people, some of which are members of Hailu’s party, in bars around Silver Spring, Maryland, that are located in front of borders, such as “Galaxy” (I hope some residents of DC, Maryland, and Virginia understand the specific location which I am talking about). These people always seem in some kind of intrigue. I do not believe that every “Tigre” is “Woyane”. But I am very suspicious of one of the “Tigirigna” speaker that I found always with Admasu and his colleagues. In fact, I am very suspicion of Mr. Admasu even when I was in Ethiopia. Nevertheless, what the writer states is a serious allegation, which would turn into defamation if he does not present the evidence that he claims to have. Besides, I think EMF should not take the road that “Elias”(ethiopianreview) has already taken.

    30. Good_Job Says:

      I know most us are worried about “what if this is not true ?”
      we can equally ask “what if it is true” .My suggesion is send
      ER’s team to investigate ,they are good at it.specially about the house he is having as a parliamentarian which is relatively easy to verify and the other issues in the article.
      Till then watch out ……..

    31. Kerim Says:

      From z very beginning the writer is from KIC (ከይሲ), a group who worked tirelessly in dismantling our party (Kinijit) under z leadership of Hailu Shawel & Taye. Next, what he is allegating his banda collegue is a trash (የመንደር ወሬ) which is a shameful act normal for idiots. Finally the truth is coming & evry KIC member is exposing him self & his collaborator.

      Victory for UDJ!!!!
      Victory for G7 & Ethiopia!!!!!!

    32. Anonymous Says:

      ይህ አይነት አክራረብ ስም ከማትፋት የዘለለ አይደለም::እባካችሁን ትምህርት ሊሰት የሚችል ኩም ነገር አስተላልፉ:: መሰረት ቢስ ነው ምክንያቱም ማስረጃ የለውም

      ከበደ

    33. degu Says:

      የወሬ ቅራቅንቦና ጹሁፍ የለያዩ ነገሮች ናቸው:: ኤምፍ ታብሎይድ መሆኑን አቁሞ ቁም ነገር ቢያወራ ያዋጣዋል:: :-) ቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂቂ

    34. ሃበሻ Says:

      የማይረባ ወሬ ትተን ያለብንን ፈተና ብንወጣ ምን አለ? ለመሆኑ የዚህ ንባብ ደራሲ የት ነበሩ? እስከዛሬ ምነው አልጮሁም? ነው ወይንስ ከሻለቃው ጋር ተጋጩ?ነው እሳቸውም አብረው ሰላይ ነበሩ? ይገርማል እኮ ባካችሁ እስከመቼ ይሆን ትልቁም ትንሹም ሚዲያውም ስራ የሚፈታው? አገር ተቆረሰች ወሬ ሰው ተገደለ ወሬ ምን ይሻለናል? ታዲያ ምን ይገርማል ወያኔ ቢያሸን ማን ከልክሎት እኛ የወሬ አቊማዳ፡ስንሞላ?

    35. ashu Says:

      I can’t immagine u still talk and post such a useless article

    36. Hola Says:

      አስቀድሞ ነበር መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ:: እኔ የማይገባኝ አሁን….እኝህን ሰውዬ እንዲህ ነው እንዲያ ነው ብንል ምን ዋጋ አለው? የታወቁ አጭበርባሪ ባንዳ እንደሆኑ ከታወቀ ሰነባብቷል:: ስለዚህ ከአሁን በኋላ መሆን ለሚገባው መነጋገሩ ይበጃል:: አዛውንቶቹ ደግሞ ወጣቱን ኃይል አትናቁት… እንደዚህ ዓይነቱን አወናባጅ በስሌት ይይዘዋል::የወጣቱን ኃይል ለመጠቀም መሞከር ነው::

    37. Anonymous Says:

      ይህ ሻለቃ ከእንግዲ በተቃማዊዎች የሚያመጣው ጉዳት የለም:: በወያኔ የተላከበትን ቅንጅትን የማፈራረስ ስራ ሰርቶ ጨርሷል::

      ሻለቃውን ለጎሪጥ እየተከታተል የረባ ያረባው እያዎራን ጊዚያችን ከምናጠፋ ይልቅ ወደ ዋናው ወያኔን የመታገል ስራችን ብንሰራ የተሻለ ነው::

      ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ::

    38. Hagos Araya Says:

      Thanks for the information, however the shaleqa and the horrible hailu shawel branch that was created in the command in chief of Eyasu EPRP members are gone, they are all history. We all forgot their poor and trash game, however we won’t forget that the Hailu Shawel group and shaleqa admasse worest job that had killed the Ethiopian struggle for a moment. To me it was not only the shaleqa and other ruminants of KIC in north America, it was Hailu shawel’s big mistake to associate him self with the corrupted KIC groups of shaleqa yoseph, dedeb taye and others including EYASU EPRP that had dragged and hurt the struggle. Anyway, forget the so called shaleqa and hailu shawel, lets support the best parties at a moment UDJ and GINBOT 7……
      Go G7 go………death to weyane members and supporters.

    39. Kebe Says:

      Hanni,

      I know the area you are informing us. I have also seen Major Admassu Melaku many times places such as Omo Restaurant on Sligo Avenu, in Silver Spring, MD. He likes to drink and it is good to know that he is addicted to Silver Spring area bars.

      I have come to conclude that Major Admasu and Compatriot Lidetu are cowards and insiders of the tplf mafia within AAPO. Of course there are others too. And let’s wait each one of them being closed up day after day.

      Cher Yigtemen!

    40. tedi Says:

      When I was in Ethiopia,i suspicion Shel.Adamasu.when we were in AApo,LIdetu(kidetu)suspected him.Because they know each other.when he came to U.S.a with DR. bezabe,I don’t support them.that is why i don’t trust KIC. God bless ETHIOPIA. down waynae and banda Eyasu’s EPRP long live Andant party, G 7 and ECADF pal talk room

    41. LULU Says:

      እና ምን ይሁን ? የታለ ማስረጃው ? ኢኤምኤፍ ይህን እንደ ማስረጃ አምኖበት ተቀብሎ ነው የኢንተርኔት ድረ ገጽ ላይ ያወጣው ? ምናለ ከእንደዚህ ያለ ገለባ ወሬ ብንርቅ? ሰውየውን ክፉ አድርጎ ከአግባብ ውጪ የሰራው ተንኮል ካለ ጥርት ባለ ሁኔታ በወቅቱ ማጋለጥ ነበር ነገር ካለፈ በሁዋላ ማንንም ሊጠቅም አይችልም !

    42. Dawit Says:

      I know some facts about Shaleka Admasu.He wants to destroy Kinijit with help of Bedru Adam.If any of you have healthy mind,how Shaleka Admasu be allowed to go to USA with Dr.Bezabih through the red carpet of Bole Airport while his colleagues were in prison?I was close to him for sometimes and concluded that he is anti unity.It is good to reveal facts.He is staying in the USA until he finishes the Mission.

    43. Gen shoaregede gedele Says:

      All the shameless hoadams and bandas will face justice including Eyassu’s servant hode adre taye , who has worked /served TPLF by working day and night to dismantle kinijit both in diaspora and in ethiopia.Believe me both hodams under the leadership of HAilu shawul are working hand in clof with weyanes. Let me give you one evidence about admasse’s and hailu’s service for TPLF. when hodam yosef and his gangister group suspened ato andrgachew and ato Birhane mewa,and later selfish and power monger hailu suspened five top kinijit’s leaders , both suspentions statement release by one of weyane’s web sites [on AYIGA FORUM] how could these happened ? who gave the suspentions or the bloody hodam’s decissions statement for Ayiga forum before they release by their trash web site? The dead fish hailu has closed by radios to fill full his commitement and support weyanes.That is not enough, Hailu has legalized the former AAPO, the later AEUP,[which Hailu considred as his own business company] as soon as he left qality, and left USA and styaed there more than 9 months, when he returned from USA, he and his dogs went to weyane’s court to claim CUDP, which means the second legal party .Hailu wanted to be the leader of two legal parties, 1, the leader of AEUP, which he has legalized as soon as he was released from qality and 2, CUDP. All these weyanes dramas. weyanes have showed the copy of Hailu’s legalized party’s name [AEUP] , told all his allies like yammamoto that HAilu wants to have two legal parties at a time. they are laughing at this political ignorant person for his arrogancy. So it is very difficult to have a good egg from spoiled eggs, because they are both spoiled, Hailu and his dormant and hodams servants are all spoiled eggs

    44. almaz Says:

      hello EMF.

      You never wrote anything positive about AEUP in the past. Why now when something negative?
      why doesnt the writer expose himself first? where is the evidence?
      I do not trust the writer at all because if he believes he has evidence he must tell us who he is in the first place. Publishing Personal information about what kind of car he drives and about his wife is too cheap!

    45. Anonymous Says:

      በጣም ነው የምትገርሙት

    46. Anonymous Says:

      ጊዚያችሁን በአሉባልታ አታትፉ::ማስረጃ የለለው ክስ ውድቅ ነው:: ያልተጨበጠ ወሪ ማቅረብ ይቅርባችሁ:: ስለኢትዩጵያ ብላችሁ የግለሰቦችን ስም ማትፋት ይቅርባችሁ
      አምላክ ይባርካችሁ
      አሚን

      አቢቱ ተዘከረነ

    47. tenesae Says:

      tedy I agree with you , I suspected him(shal.Admasu),when I was back home .He knows how to pretend.some henosant people and his relativea ask evidance.The big evidanece is to dismantale Kinigit,after that he ask asylam. God bless Ethiopia
      Death Wayane , hodam and Eyasu’sEPRP
      Long live Andant Party,G7, and ECADFpaltalk room.

    48. Tagel Says:

      አንድ ሰው አንድ ጊዜ ሲያታልልህ የሱን ብልጠት ያሳያል ሁለተኛ ከደገመህ ግን የአንተን ጅልነት ነው የሚያመለክተው:: ያም ሆነ ይህ ወያኔ እንዴት ሁል ጊዜ ተቃዋሚዎቸን በተራ ሰዎች እንዲህ መጫውቻ ያደርጋቸዋል:: ከሆነም ይህ የራሳቸው ድክመት መሆኑን በቅድሚያ ማወቅ ጠቃሚ ይመስለኛል::

    49. snshaw Says:

      ወያኔ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ በውጭው መድቦ ኢትዮጵያውያንን ለማመስ የተያያዘበትን ጎዳና ከሚያጠናክሩ ወገኖች መካከል እንደዚህ የመሳሰሉት በየወቅቱ ብቅ እያሉ በመሰላቸው ጉዳይና ግለሰብ ዙሪያ በአስረሽ ምቺው ሲዘምቱ ይህ የመጀመሪያቸው ባለመሆኑ ብዙ ሊደንቀን አይገባም ግና ያዘጋጁልን የአልባልታ ድግስ ጨርሶ በታትኖን እስኪያስቀረን የሚቀጥል ነውና ሁሉንም በትዕግስት መጠበቅ ብቻ ነው::ትናንት በተለያየ ጎራ ተመዳድበው በወገን ውስጥ ተሰግስገው በዶክተር ታዬ ብርሀኑና በኢንጅነር ሀይሉ በመሳሰሉት ላይ ሌት ተቀን በአሉባልታና ስም ማጥፋት በመዝመት የወገንን ሞራልና ስሜት ማዳሸቃቸው እየታወቀ ዛሬ ተነስተው ደግሞ ከዚህና ከዚያ ወሬ እየገጣጠሙ የለመዱትን ተግባር ሲናኙበት እየታዘብን ነው::
      ሆኖም ወገን እነዚህን የመሳሰሉ የቀን ጅቦች ላይ አንድ ቀን በትሩን ማንሳቱ አይቀሬ ነውና ያኔ ወያኔ ያሸከማቸው ብር ምሽግ ሆኖ ያድናቸው እንደሆን ግዜ የሚያሳየን ይሆናል:: እስከዛው ወገን በያለበት ይህንን የጥፋት ዘመቻ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በእንዴትና በምን አይነት ሁኔታ መምታትና መቅበር እንደሚገባ የጀመረውን ስራ በበቂ ደረጃ አጠናክሮ እንዲቀጥል ይህ ተጨማሪ ሀይል የሚፈጥርለት በመሆኑ እግረመንገዱን ዘረኛና ጎጠኛውን የወያኔ አገዛዝ ለመታገል የሚያስችለውን አቅሙን እየገነባ ወገን በቅርቡ የማያዳግም እርምጃ እነዚህንን በመሳሰሉ የወያኔ ተላላኪዎች ላይ እንደሚወስድና በዚህም ለበርካታ ሆዳሞች የማያዳግም ትምህርት እንደሚያስተላልፍ ለጸሀፊው ግልጽ ማድረግ ያስፈልጋል::

      በወገን ስቃይ መነገዱ
      በወገን ርሀብ መጥገቡ
      በበሽታው መዳኑ
      በእንግልቱ መራቀቁ የሚቆምበት ወቅት ሩቅ አይደለም

      ወያኔ በህዝብ ትግል ከህዝብ ጫንቃ ይወገዳል
      ስንሻው

    50. koleelu Says:

      This articles more how much EMF and the writer are so low than Shaleka Admassu. አሉ አሉ አሉ ብቻ!! Shame

    51. Abebe Says:

      That is way i dislike CUD from day one all of them are the some not only this individual.

    52. MIKIAS Says:

      Why You Some of ppl be very defensve about shaleka,we all remember what they have done shaleka & mr.hailu to ‘cud”

    53. jambo Says:

      እባካችሁን ግዚያችንን በአሉባልታ አታጥፉብን እርስበርስ ስትባሉ ወያኒ ቀደማችሁ ሳየዉ ከወያኒ የተሳለ ስራ የመስራት ችሎታ ኖርዋችሁ አገር ትመራላችሁ ብየ አልገምትም ስለዚ በማስትዋል ፖለቲክስ ብስሉ

      ጃምቦ ከሎንዶን

    54. slugger Says:

      These are all crooks. Hailu Shawel, Lidetu ayalew, this guy and others like them are no better than Meles Zenawi. The biggest crook of all is Hailu Shawel. He was the friend of killers like Fikreselassie Wegderesse. Now he changed cloth and appeared like a different person. My question is what were modern people like Berhanu, Birtukan, fekadu, yakob, etc were thinking when they joined with such a double face criminal like hailu shawel to form a party. Hailu Shawel doesn’t even understand the complexity of Ethiopian politics.

    55. እ ያ ደ ረ ይ ጠ ራ ል Says:

      እውነቱ ተሠማ እንደ ሁሊም ሥም የማጥፋት ዘመቻውን ተያይዞታል
      እግዚኦ የሚያስጘ ነው ጃል፡

    56. yonas Says:

      እንደዚህ እያላችሁ ዘላለም እየተባላችሁ ኢትዮጵያ የማትወጣበት አዘቅጥ ውስጥ ከተታችኋት:: እናንት አሮጌ ትውልዶች ሙታችሁ ካላለቃችሁ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ማየት አንችልም:: ውድ ጸሃፊ ሃቀኛ ከሆኑ እንድው ትክክለኛ ሰምዎትን ከግርጌው መጻፉ ምን አስፈራዎ???????????

    57. junneye Says:

      በጣም የሚያስቀው ካወራው ሰው በላይ የተቀባዩ ነው:: ይህን ያህል ዘቕጠን ከሆነ ወያነ እኛን መግዛት ሲያንስው ነው:: ሰውየው ምንም ሊሆን ይችላልኣድማሱ):: ሌላው ቢቀር እንደት አንድ ማስረጃ ሳይጠቅስ 10 አሉባልታ አውርቶ 10 ማስረጃ አቀረብኩ ሲለን,.. ምን ያሀል ቢንቀን ይሆን? አቦ በቃን እንበል ይህን የስቢሰቲ ዘመን ፖለቲካ, የማኪኤን’ን ፖለቲካ ትተን እንደ-ኦባማ ማሰብ እንጀምር አቦ ,…መከራችን ይብቃ,.. ጸሃፊው ግን ይገርማል:: ካንተ በላይ ደግሞ ተቀባዩ,……ኪኪኪኪኪኪኪኪኪ የዲሲውን ጋዚጠጝና ንጉሲት ወ/ማሪያምን አሰታወሰኝ:: ኪኪኪኪኪ

    58. Anonymous Says:

      KETAFE HULA MANEM YEMEYAMN YELAM ,EYAMERATACHU SEM ATFU ENMAN ENDA HONACHU ENAWKALEN YENNTA GUD BAKERBU YEWATLE