- በህይወት የሌሉ “የቅንጅት” ተወካይ በአዲስ አበባ ምርጫ አሸነፉ
- የፓርላማ ተመራጮች በቀዝቃዛ ወለል ጫማ ያወልቃሉ
Sunday, 04 May 2008 — ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት ምርጫ የቅንጅት ፓርቲን ወክለው በመቅረብ በቦሌ ክፍለ ከተማ ከተቃዋሚ ፓርቲ በብቸኝነት አሸንፈዋል የተባሉት እጩ በህይወት የሌሉ መሆናቸው ተገለፀ፡፡ ምርጫ ቦርድ በጉዳዩ ላይ አስተያየት መስጠት አልፈለገም፡፡
ሚያዝያ 5 ቀን 2000 ዓ.ም በአዲስ አበባ በተካሄደው የአካባቢና የማሟያ ምርጫ የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ በቦሌ ክፍለ ከተማ ለአዲስ አበባ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት ምርጫ ያቀረባቸውና በውድድሩ 6 ሺህ 37 ድምፅ አግኝተው፣ በአዲስ አበባ ብቸኛ ተቃዋሚ ፓርቲ አሸናፊ መሆናቸው ይፋ የተደረገላቸው ወ/ሮ ቦድዲት አንተነህ ቡጀቴ በሕመም ምክንያት ካረፉ ከ26 ቀናት በላይ ተቆጥረው ነበር፡፡
የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ዋና ፀሐፊ አቶ ሳሳሁልህ ከበደ ወ/ሮ ቦድዲት አንተነህ ምርጫው ከመድረሱ በፊት ከዚህ አለም በሞት መለየታቸውን ፓርቲው በደብዳቤ ለቦርዱ ማሳወቁን ይገልፃሉ፡፡ ይህንንም ጉዳይ በተመለከተ ለምርጫ ቦርዱ በቁጥር ኦዴፓ/208/2000 በቀን 16-07 - 2000 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ማሳወቃቸውን የሚገልፅ ግልባጭ ለዝግጅት ክፍላችን ልከዋል፡፡
በአቶ ሳሳሁልህ ገለፃ መሰረት ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት በተፃፈ ደብዳቤ ወ/ሮ ቦድዲት አንተነህ ቡጀቴ መጋቢት 9 ቀን 2000 ዓ.ም በህመም ምክንያት ከዚህ አለም መለየታቸውን ተገልጿል፡፡ ፓርቲው በደብዳቤው በዚህም ምክንያት በምርጫ ሕግ አዋጅ ቁጥር 532/99 አንቀፅ 55 መሰረት ተተኪ እጩ መመደቡንም ገል..ል፡፡
ዋና ፀሀፊው በደብዳቤው በወ/ሮ ቦድዲት ምትክ፣ ወ/ት ትዝታ ጌታሁን በቦሌ ክፍለ ከተማ እንዲወዳደሩ አሳውቋል፡፡ “ይህ እንዲህ ሆኖ ሳለ” ይላሉ አቶ ሳሳሁልህ “የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማስተካከያ ሳያደርግ ቀርቷል”፡፡ በዚህም ምርጫ ቦርድ ባወጣው የምርጫ ውጤት ላይ ወ/ሮ ቦድዲት 6 ሺህ 37 ድምፅ በማግኘት ማሸነፋቸው መገለፁን ጠቁመዋል፡፡
አቶ ሳሳሁልህ በምርጫው ቦርድ ስህተት ምክንያት ፓርቲው ያገኘው ድል ሊሰረዝ እንደማይገባ አሳስበዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ በውድድሩ 5993 ድምፅ ያገኙትን የፓርቲውን እጩ ተወዳዳሪ ዶ/ር ለምለም መኮንን እንዲያሳልፍ ዋና ፀሐፊው አሳስበዋል፡፡
የመኢብን ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ መስፍን ሽፈራው በበኩላቸው በምርጫው ውጤት ላይ በቅንጅት ፓርቲ ወይም በምርጫ ቦርድ ምክንያት ስህተት መከሰቱን ጠቁመው፤ “የምርጫው ውጤት ሙሉ ለሙሉ ተሰርዞ በጣቢያው የመኢብን እጩ የሆኑት ወ/ት ገነት ይማም ወለሎ ሊያልፉ ይገባል” ሲሉ አቋማቸውን አስታውቀዋል፡፡
በምርጫ ጣቢያው የተከሰተውን “ስህተት” በተመለከተ በአዲስ አበባ የምርጫ አስተባባሪ አቶ ደስታ ሀ/ሚካኤል ተጠይቀው የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት በጉዳዩ ዙሪያ ውሳኔ ለመስጠት እየተወያየ መሆኑን ከመጥቀስ ውጪ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡
በሚያዝያ 5 ምርጫ ለአዲስ አበባ አስተዳደር ም/ቤት በቦሌ ክ/ከተማ ኢሕአዴግ ያቀረበውን ዕጩ በመሠረዙ ምክንያት (በፎርፌ) የቅንጅት ፓርቲ ዕጩ ማሸነፋቸውን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
የፓርላማ አባላት በመግቢያ ፍተሻ ተማረዋል
Sunday, 04 May 2008 — የተቃዋሚ ፓርቲ የተወካዮች ምክር ቤት አባላት በምክር ቤቱ መግቢያ በር ላይ በሚካሄደው ፍተሻ “የሚያዋርድ” መሆኑን በመጥቀስ ቅሬታቸውን ለሪፖርተር ጋዜጣ ገለፁ፡፡ የምክር ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ኦፊሰር በበኩላቸው የሚካሄደው ፍተሻ አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የኢዴኅህ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ፍተሻውን አስመልክተው ሲናገሩ “ሕዝብ መርጦ ይወክልናል፡፡ እዚህ ያሉት ደግሞ ያወርዱናል” ሲሉ የምክር ቤት አባላት አላስፈላጊ መንገላታት ውስጥ እንደሚገቡ አብራርተዋል፡፡የኢሕአዴግ ባለሥልጣን የሆኑት አንዳንድ የፓርላማ አባላት ሳይፈተሹ መኪና ይዘው በሌላ በር እንደሚገቡና ሌሎች የፓርላማ አባላት ግን ንጽህናው ባልተጠበቀ የሲሚንቶ ወለል ላይ ጫማቸውን እንዲያወልቁ፣ ቀበቶዋቸውን እንዲፈቱ እየተደረገ የሚዋረዱበት ሁኔታ መኖሩን ኘሮፌሰር በየነ አስረድተዋል፡፡ “በዚህም” ይላሉ ኘሮፌሰር በየነ “በሕዝብ እንደራሴዎች መካከል የሚታመንና የማይታመን እንዳለ ነው ሊነግሩን የሚፈልጉት” ካሉ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የደህንነት ጥበቃም አለም ውስጥ ካለው ሁሉ ገንኖ እንደሚወጣ ገልፀዋል፡፡
የመፈተሻ መሳሪያውን በተመለከተም ፕሮፌሰሩ ቅሬታ አላቸው፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት መዳብና ጥቃቅን ብረታ ብረቶች ሳይቀር የመፈተሻ መሳሪያውን ማለፍ አይችሉም፡፡
በፍተሻው ሂደት ላይ የሚታየውን ውርደት መቀበል የማይፈልግ ሰው፣ ወደ ፓርላማ የመሄድ ፍላጎቱ እንደሚቀንስ የገለጹት ፕሮፌሰር በየነ፣ በጣም አስፈላጊ ካልሆነ በስተቀር የተቃዋሚ ፓርቲዎች የምክር ቤት አባላት ወደ ፓርላማ እንደማይሄዱ በዚህም ተሳትፏቸው እየተገታ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
“ጫማ እንድናወልቅ የምንገደድ ከሆነ፣ በስጋጃ ምንጣፍ ላይ ቆመን የምናወልቅበት ሁኔታ መመቻቸት ነበረበት” ያሉት ፕሮፌሰሩ እንደራሴዎቹ ጫማቸውን የሚያወልቁት ሲሚንቶ ወለል ላይ መሆኑ ችግር እንደፈጠረ ተናግረዋል፡፡
የሌሎች አገሮችን ሲናገሩም በአሜሪካ ያለው የፓርላማ ስርዓት የሕዝብ እንደራሴዎች ወደ ምክር ቤት የሚገቡበት የተለየ በር እንዳላቸውና ሌሎች ተመልካቾች ግን ተፈትሸውና መታወቂያ አስቀምጠው እንዲገቡ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡
ፕሮፌሰሩ እንደሚሉት አሜሪካ ያለችበት ደረጃ ላይ ይደረስ ባይባልም አሁን ያለው የፍተሻ ሂደት መስተካከል አለበት፡፡ አያይዘውም “በሌላ አገር የሚገኝ አየር ማረፊያን የደህንነት መቆጣጠሪያ አልፈን የምንሄድ ሰዎች እንዴት ይህንን (የፓርላማውን መፈተሻ) አልፈን መሄድ ያስቸግረናል” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
የኦፌድን ሊቀመንበር አቶ ቡልቻ ደመቅሳም የፕሮፌሰር በየነን ሀሳብ ይጋራሉ፡፡ ስለፍተሻው ሲናገሩም “በር ላይ ተዋርዶ የገባ ሰው አስቦ መናገር እስኪችል ድረስ ደቂቃዎች ይወስዱበታል” ብለዋል፡፡ የፍተሻው ሁኔታ ሁልጊዜ እንደሚያስደነግጣቸው የሚናገሩት አቶ ቡልቻ 100 ሺህ ሕዝብ የሚወክል እያንዳንዱ የፓርላማ አባል ጫማውን እያወለቀና ቀበቶውን እየፈታ ሲዋረድ ማየት የሚያሳዝን ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
Source: Reporter


May 5th, 2008 at 4:15 pm
No need of going to this crap parlament.Please, stayaway and do something valuable for your people and the nation .Being in parlament has no use except giving some cover for woyane`s dictatorial regime.
May 5th, 2008 at 4:30 pm
This is not an unexpected incident as tplf is a collection barbarian people who rule the country for the last 17 years with a jungle law and rule of gun. All Ethiopians and the world wittiness that woyane have been ridiculing Ethiopian sovereignty, justice, freedom, and human rights in the country.
May 5th, 2008 at 4:56 pm
እናንተ ቅሊታሞች የሂም ሲያንሳችሁ ነው ደሞ ዐፍ አለን ብላችሁ ታወራላችሁ ማፋሪያዎች
May 5th, 2008 at 5:41 pm
Woyane is the 21 century funny creature
May 5th, 2008 at 6:13 pm
Wedesh ketedefash, biregtush ayikfash…what less do these condoms expect or hope from such decadent and irresponsible gang? We throw the used condom to the garbage bin but this gang makes the condom remove its smelly shoes! I have never encouraged nor supported this mafia and its action. Cheers! You know, even tyrants do somethings right! Kechuhawoch and alehu bayoch andande qum neger aytattam, ale terguwamiw!!!!
May 5th, 2008 at 6:19 pm
Beyene Petros said this
Bulcha Demeksa said this It is simply talk
They are nothig for the Ethiopian people.
ማፈሪያዎች ናችሀው!!!
Woyane used them and thrown them away. Kelas!!!!
May 5th, 2008 at 9:11 pm
ገና ፓንትህን ታወልቃለህ ወራዳ ቀበቶማ ድሮ ፓርላማ የገባህ ግዘ ነው የወለቀዉ ሙትቻ
May 5th, 2008 at 11:32 pm
I have the feeling that all the news posted on pro-democracy websites such as this one should be about the vast loaf of land that is presented to dictator albeshir as a favor for his unprecedented effort to destroy ethiopian opposition making movements in the sudan boarder.
Ethiopia is being sold piece by piece and u are posting creepy news from woyane-tigray controlled mafia news paper!!
Ethiopians need timely info. about the boarder situation and that should be ur priority, our priority off course!!!!
May 6th, 2008 at 2:03 am
I am sorry to hear that from those two tamagn tekawamiwoch……shame on you!!! since woyane found ayele chamiso, you are no longer important …….. maferiawoch. you should hung yourself.
May 6th, 2008 at 3:38 am
በህዝብ ከምትጫወት እንዲሁም ከመረረህ ለምን እንደ ቀድሞዎቹ ቅንጅቶች አትቀርም? አጋሰስ! ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ ይላል ያገሬ ሰው
May 6th, 2008 at 6:00 am
Dear brothers
Beyne and Bulatch They are good for nathing .do not expect from them any thing..Bulatch is running for ego.Beyne is living for parliment salary.they have no stand at the same time.when one get a good chance he will bettry his commrade for simple advantage.
May 6th, 2008 at 7:40 am
ቅሌታሞች, ይህም ሲያንሳችሁ ነው:: ልብሳችሁን አውልቃችሁ ራቁታችሁን ባቆማችሁና በተፈተሻችሁ.
May 6th, 2008 at 9:06 am
ዶ/ር በየነ፣ አቶ ቡልቻና መሰሎቻችሁ እናንተን የመረጣችሁ እኮ ሕዝብ ሳይሆን ወያኔ ነው የመለመላችሁ ወይም የቀጠራችሁ:: አንድ ምልምል ወይም ተቀጣሪ ደግሞ በጌታው እንዴት ይታመናል:: ከእርሱ የበለጠ ዋጋ የሚሰጣችሁ ባላንጣ ቢሊክበትስ ምኑ ሞኝ ነው መለስ! ስለዚህ አድርጉ ያላችሁን መቀበልና ፍርፋሪ መልቀም ወይም መልቀቅ እንጂ ሀሜቱ ምን ባይ ነው:: የኢትዮጵያ ሕዝብ እኮ ቁሽቱ የሚያረው በእናንተ አሻንጉሊትነት እንጂ ወያኔማ… ዛሬ ብላ ነገ ትሞታለህ… ብሎ ከመጀመሪያወም የተነሳ የሰው ጅብ ነው:: . . . ጠላትማ ምን ጊዜም ጠላት ነው አስቀድሞ መግደል አሾክሿኪውን ነው. . . ይባላልና የምትነግዱበት ሕዝብ አንድ ቀን ሳያጠፋችሁ ወይም ወያኔ ሳይዉጣችሁ እስኪ የእነ ሺህ ብሬን ልብ ግዙ ! ኝስሐ ግቡ! ኃጢያታችሁ ለዘራችሁ እንዳይተላለፍ እንኳ……
May 6th, 2008 at 2:45 pm
Never count on “ethiopian opposition group”. We need to find a solution ourselves, each of us should come up with an idea that we think best works to topple zenawi’s tyranny.
I for one believe that assasinating zenawi and then terrorizing the lower level woyane goons by physically attacking their family members and implementing a well designed social descrimination against the woyannes can be fruitful.
But to coordinate such actions trustworthy leaders are imperative, we need such leaders to coordinate the meagre indivisualistic efforts to a wave of public force to outset zenawi and his tigray relatives out of our country.
One way to pursue the above mensioned startegy is to align the diaspora movement with the ARMED FORCES that are functioning in the peripheries of ethiopia. But again to do this we need to get information as to the aim of these groups and we need to identify and work with only those that can serve the GOOD OF ETHIOPIA AND ITS PEOPLE!!
To hit on my points once again, to weaken woyane and later topple it:
1. assassinate zenawi, through contracted assassinators.
2. exercise effective discrimination and physical attack on family members of woyane thugs!!
May 7th, 2008 at 6:01 am
ህዝቡ አሁንም ቢሆን በቁሙ ሞቶ አልሞትኩም ከሚል ወያኔ
የማይቀርለትን ሞት የሞተ የቅንጅትን ተወካይ ያምናል
May 7th, 2008 at 12:23 pm
you will never be free of us ! So why bother fighting your destiny, just embrace it !
When I say fight , I don’t mean that you will ever be man enough to fight us..I meant , stop talking about it every web-site ,stop kidding urselfs. Face it ..you all are cowards ! You all have been crying every corner of the world. You want the white man to free you ,is that it?.. What a shamfull people you all are !… We fight like a man and look us where it gotten us ! We only hope that you fight us like a man so we could show you once again who the man is.
Bunch of sisi’s.
May 7th, 2008 at 1:38 pm
በቅድሚያ የሞቱትን ተመራጭ ነብስ ይማር እላለሁ:: እንዲያው ለወጉ ነው እንጂ ያሉትና የሞቱት ልዩነታችው አንዱ ከመቃብር በላይ ሌላው ከመቃብር በታች መሆናቸው ብቻ ነው:: “አምና ነበር እንጂ ዘንድሮ የለህም” እየተባለ ምኒልክስ ገዝትው አልነበር!! ነገርን ነገር ስላነሳው ነው እንጅ ልዩነቱ እገባኛል..
May 7th, 2008 at 2:28 pm
ኡመር:
በጣም ቆንጆ አባባል ነው::
May 7th, 2008 at 4:20 pm
አፍ አለን ብለው ያወራሉ. በተለይ በየነ የሙህር አድር ባይ …. ጉዋደኞቹን አሳስሮ ፓርላማ የገባ …. ዛረ ወይ ከ ወያኔ ወይ ከ ህዝቡ ጋር ያልሆነ…. ኢትዮጵያ የማትወልደው ጉድ የለም.
May 8th, 2008 at 12:55 am
kill meles on contracted assasins? what a bunch of sisi’s!
Amara bedn hone.
May 9th, 2008 at 11:51 am
ኣይ የናንተ ነገር: ወደ ወልቃይት በረሃ ጎራ ማለት ነዋ: እዛ ፈተሻ የለ ዉዥንብር: ለሃቅና እኩልነት እንደ ወንድ መታገል:
May 9th, 2008 at 4:30 pm
የሞተማ ሞተ!
ለፍትህ ለዲሞክራሲ…
ለተስፋ አገር ሕይወት
ለእንዲት ኢትዮጵያ!
ምትክ ለሌለላት
የሞተማ ሞተ!
አምና ወዲያ…ወዲያ…
ወዲያ-ኝያው ካቻምና
ካ-ፈር ተከተተ::
የካርዼን ማሕተም…
ድሌን አምቢኝ! ብሎ
በጎዳና ተሞ…
ቃሉን- በቃል ስሎ
በዼሙ ፈር ጥሎ!
የሞተማ ሞተ…
ካ-ፈር ተከተተ::
ያለነው ነን እንጅ…
‘ንዳለን ያልሆንን
ውሃ ‘ ንዳላየ መሬት…
ስን-ትር-ትር ብለን
ሞት የማይሉት ” ሞት”
በቁም ያሸለብን::
May 18th, 2008 at 7:25 pm
[…] ‘opposition’ won only one seat in Addis Ababa, and the guy is not even alive, as reported by The Reporter. The election was a total […]
May 22nd, 2008 at 5:01 pm
[…] are also complaining that they are being degraded by the ruling EPRDF. They are compelled to take their belts and shoes off on a very cold floor for every session. “The people honourably elected us but the regime is […]
May 24th, 2008 at 2:26 am
ወደሽ ከደፋሽ ቢረግጡች አይክፋሽ ብለናል ፐሮፊሰር በየነ ነጻ እናዎጣዋታለን;;አያላዝኑ…ለሆዳም ቀበቶ አይስፈልገውም …